በየኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን (EMWACDC) አዘጋጅነት በባህርዳር ከተማ የ አንድ ቀን ወርክሾፕ ተካሄደ

📍 ባህርዳር 📅 Apr 07, 2026
Main News
በየኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን (EMWACDC) አዘጋጅነት በባህርዳር ከተማ የ አንድ ቀን ወርክሾፕ ተካሄደ ።\r\nየኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን (EMWACDC) ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በ ባህርዳር ከተማ  አሲኗራ ሆቴል \r\nሁለንተናዊ አገልግሎት በሚል ርዕሰ \r\nየውጭ ጥገኝነትን  መጠበቃችንን ትተን በእጃችን ያለንን ሀብት በማሰባሰብ ልማትን ለማፋጠንና  አቅመ ደካሞችን ለመርዳት የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር በመሆን ተገቢ መሆኑን በማስገንዘብ   የአንድ ቀን  ወርክሾፕ ተካሂዷል። \r\nይህ ወርክሾፕ፤  በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ወንጌላዊያን አማኞች አብያተ ቤተ ክርስቲያናት መሪዎች እና አገልጋዮች ድሆችን ለማገልገል ከውጭ ሀብት ማግኘት አለብን የሚለውን ሀሳብ ያስጣለ እና ቤተክርስቲያን ያላትን ሀብት በማቀናጀት መስራት የምትችለው  ከጌታ ኢየሱስ የተቀበለችው አደራ እና እውነተኛ አምልኮ መሆኑን ያሳዬ እና ከፍተኛ ተነሳሽነትን የፈጠረ   ወሳኝ መድረክ ሆኗል ። \r\nበዕለቱ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው እና የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፓስተር ብርሃኑ ታረቀኝ የተገኙ ስሆን ፤\r\nፓስተር ለወየሁ ከመፅሐፍ ቅዱስ ከፍል ላይ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1-3 ላይ ያለውን መሠረት በማድረግ \" የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር ሁን\" በሚል ለጉባኤው ተሳታፊዎች የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል :\r\nመጋቢ ለወየሁ ስንሻው ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህን መልዕክት ሲፅፍ የነበረበትን ሲገልፁ: ይህ መልዕክት የመጨረሻው እንደሆነ እና በብቸኝነት ውስጥ ሆኖ የፃፈው ሲሆን መልዕክቱን ያስተላለፈበት 2 አብይ ምክንያቶች :\r\n1. የቤተክርስቲያን የውጭ ተግዳሮት እና\r\n2. የቤተክርስቲያን የውስጥ ተግዳሮት እንዳለባት ለጢሞቴዎስ ለማሳሰብ እና በእነዚህ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ እንዲበረታ እና ሊመጣ ላለው ችግር እና መከራ እንዲበረታ ለማስቻል ነው ብለዋል።\r\nበጋቢው አክለውም ወታደርነት:\r\n1. የአዕምሮ ጥንካሬን የሚጠይቅ ፣\r\n2. ስነ-ምግባራዊ መሰረት ያለው መሆን፣\r\n3. ተግባራዊ ክህሎትን የሚጠይቅ:\r\nመሆኑን በማውሳት የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር ሊኖሩት የሚገባ ባህሪያትንም ጨምረው አስቀምጠዋል። እነሱም:\r\n1. ባለ አደራ መሆን፣\r\n2. የጌታን ህይወት መካፈል፣\r\n3. ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ማለፍ ማለትም:\r\n               ሀ. መዋዕለ እኔነትን፣\r\n               ለ. መዋዕለ ንዋይን፣\r\n               ሐ. መዋዕለ ምቾትን ፣\r\n4. ተልዕኮውን መወጣት መቻል ናቸው ብለዋል።\r\nበተጨማሪም የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር \"የሰውን ሁለንተና ማገልገል\" በሚል ርዕስ ለተሳታፊዎች ስልጠና ሰጥዋል።\r\nበስልጠናው የተላለፋ አንኳር መልዕክቶች :\r\n1. የሰውን ሁለንተና ማገልገል ኢየሱስ ክርስቶስ ያገለገለው አገልግሎት ሲሆን ቤተክርስቲያን ልትሰማራበት የሚሻ መሆኑን ፣\r\n2. የሰውን ሁለንተና ማገልገል የልማት ጉዳይ ሳይሆን የወንጌል አካል እንደሆነ እና እንዲያውም እውነተኛ አምልኮ መሆኑን ፣\r\n3. ቤተክርስቲያን   ድሆችን ለማገልገል ከውጭ የሚመጣ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍን መጠበቅ እንደሌለባት እና የራሷን ሀብት እንድታይ፣ ያላትን ሀብት በማሰባሰብ ጊዜ ሳታባክን አገልግሎቱን መጀመር እንዳለባት ፣\r\n4.ክርስቲያኖች በተለያዩ ማህበራዊ ፣ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ  እና በፅድቅ በመስራት ተፅእኖ ፈጣሪ እና  ለተለያዩ በየጊዜው ለሚያጋጥሙን ማህበረሰባዊ ተግዳሮቶች የመፍትሔ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ፣\r\n5. በባህርዳር ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተናጠል ከመስራት ይልቅ በአንድነት እና በትብብር በመስራት ከክርስቶስ ኢየሱስ የተቀበሉትን የወንጌል አደራ በሚገባ  መወጣት እንዳለባቸው አጠንክረው ገልፀዋል ።\r\nከዚህ ወርክሾፕ የተገኙ ውጤቶች :\r\nበተደረገው ወርክሾፕ 105 የሚሆኑ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎችና አገልጋዮች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በእጅጉ አስፈላጊ  እና እይታቸውን ያስተካከለ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን አክለውም የሚከተሉትን ሀሳቦች አንስተዋል :\r\n1.ሰውን በሁለንተናዊ መልኩ ማገልገል(ልማት) የልማት ድርጅቶች ብቻ ሰይሆን የቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት ፣\r\n2. ክርስቲያኖች በተለያዩ ማህበራዊ ፣ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ በጎ ተፅእኖ መፍጠር እንዳለባቸው ፣\r\n3.ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ያገለገለውን ሁለንተናዊ አገልግሎት ለማገልገል ፣ ከውጭ የሚመጣን የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ(እርዳታ ) አንጋጣ ስትጠብቅ ከኖረችበት እሳቤ ወጥታ ወደ ራሷ መመልከት እንዳለባት፣ እጇ ላይ እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ሀብት ማት እንዳለባት እና ያላትን ሀብት በመጠቀም እውነተኛ አምልኮ የሆነውን የድሆችን አገልግሎት መጀመር ምርጫ የሌለው ምርጫ መሆኑን፣\r\n4. በባህርዳር ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በተናጠል ከምን ሰራ ይልቅ በጋራ እና በትብብር በመስራት ለተሻለ ለተሻለ የወንጌል ስራ እና ማህበራዊ ተደራሽነት መትጋት እንዳለባቸው በሚገባ ተረድተናል ያሉ ሲሆን በጨረሻም የተረዳነውን ተግባራዊ ለማድረግ እንተጋለን ብለዋል።